ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፤ አባትና ካህንም ሁነኝ፤ እኔም ልብሶችንና ምግብህን፥ በየዓመቱም ዐሥር ብር እሰጥሃለሁ” አለው።
መሳፍንት 17:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚካም፥ “ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም፥ “ከይሁዳ ቤተ ልሔም የሆንሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የምቀመጥበትንም ስፍራ ለመሻት እሄዳለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚካም፣ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “እኔ በይሁዳ ምድር ከምትገኝ ከቤተ ልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ መኖሪያ ስፍራ እፈልጋለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚካም፥ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “እኔ በይሁዳ ምድር ከምትገኝ ከቤተልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ መኖሪያ ስፍራ እፈልጋለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚካም “ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም “እኔ በይሁዳ ግዛት ከምትገኘው ከቤተልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የምኖርበትን ስፍራ እየፈለግሁ ነው” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚካም፦ ከወዴት መጣህ? አለው። እርሱም፦ ከቤተ ልሔም ይሁዳ የሆንሁ ሌዋዊ ነኝ፥ የምቀመጥበትንም ስፍራ ለመሻት እሄዳለሁ አለው። |
ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፤ አባትና ካህንም ሁነኝ፤ እኔም ልብሶችንና ምግብህን፥ በየዓመቱም ዐሥር ብር እሰጥሃለሁ” አለው።
ይህም ሰው በአገኘው ስፍራ ይኖር ዘንድ ከይሁዳ ከተማ ከቤተ ልሔም ሄደ፤ በዚያም ያድር ዘንድ ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት ደረሰ።