የአሮንም ልጅ ሊቀ ካህናቱ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓት መሬት ቀበሩት።
መሳፍንት 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ሰው በአገኘው ስፍራ ይኖር ዘንድ ከይሁዳ ከተማ ከቤተ ልሔም ሄደ፤ በዚያም ያድር ዘንድ ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም ሀገር ወደ ሚካ ቤት ደረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ሰው ሌላ መኖሪያ ስፍራ ለመፈለግ ከይሁዳ ቤተ ልሔም ለቅቆ ሄደ። በሚጓዝበትም ጊዜ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳለው ወደ ሚካ ቤት መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ሰው ሌላ መኖሪያ ስፍራ ለመፈለግ ከተማይቱን ለቆ ሄደ። በሚጓዘበትም ጊዜ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳለው ወደ ሚካ ቤት መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሰው የሚኖርበትን ስፍራ ለማግኘት ከቤተልሔም ተነሥቶ ሄደ፤ በጒዞም ላይ ሳለ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ወደሚገኘው ወደ ሚካ ቤት መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ሰው የሚቀመጥበትን ስፍራ ለመሻት ከከተማው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ወጣ፥ ሲሔድም ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጣ። |
የአሮንም ልጅ ሊቀ ካህናቱ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓት መሬት ቀበሩት።
ሚካም፥ “ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም፥ “ከይሁዳ ቤተ ልሔም የሆንሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የምቀመጥበትንም ስፍራ ለመሻት እሄዳለሁ” አለው።
እንዲህም ሆነ፥ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።