እኔም ከሞት ይልቅ የመረረች ነገርን አገኘሁ፤ እርስዋም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ በእጆችዋም ማሰሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ደግ የሆነ ከእርሷ ያመልጣል። ኀጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
መሳፍንት 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፍልስጥኤማውያን መሳፍንትም ሰባት ያልደረቀ ርጥብ ጠፍር አመጡላት፤ በእነርሱም አሰረችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የፍልስጥኤማውያን ገዦች ያልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች አመጡላት፤ እርሷም አሰረችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የፍልስጥኤማውያን ገዦች ያልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች አመጡላት፤ እርሷም አሰረችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች እርጥብ የሆኑ ሰባት አዳዲስ ጠፍሮችን ለደሊላ ይዘውላት መጡ፤ እርስዋም በእርሱ ሶምሶንን አሰረችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፍልስጥኤማውያንም መኳንንት ሰባት ያልደረቀ እርጥብ ጠፍር አመጡላት፥ በእርሱም አሰረችው። |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረች ነገርን አገኘሁ፤ እርስዋም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ በእጆችዋም ማሰሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ደግ የሆነ ከእርሷ ያመልጣል። ኀጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
የሚያደቡትም ሰዎች በጓዳዋ ውስጥ ተደብቀው ነበር። እርስዋም፥ “ሶምሶን ሆይ! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። እርሱም ፈትል እሳት በሸተተው ጊዜ እንዲበጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፤ ኀይሉም በምን እንደ ሆነ አልታወቀም።