መሳፍንት 16:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ሌሊቱን ሁሉ በነገር በዘበዘበችውና በአደከመችው ጊዜ፥ ልሙት እስኪል ድረስ ተበሳጨ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕይወት መኖሩን እስኪጠላ ድረስ ዕለት ዕለት በመጨቅጨቅ አሰለቸችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕይወት መኖሩን እስኪጠላ ድረስ ዕለት ዕለት በመጨቅጨቅ አሰለቸችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕለት ዕለትም እየነዘነዘች ሞቱን እስከሚመኝ ድረስ አስጨነቀችው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕለት ዕለትም በቃልዋ ነዘነዘችው አስቸገረችውም፥ ነፍሱም እስከ ሞት ድረስ ተጨነቀች። |
እግዚአብሔርም ዮናስን፥ “በውኑ ስለዚች ቅል ታዝናለህን?” አለው። እርሱም፥ “እስክሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ” አለ።
የሶምሶንም ሚስት በፊቱ እያለቀሰችበት፥ “ጠልተኸኛል፤ ከቶም አትወድደኝም፤ ለሕዝቤ ልጆች የነገርኸውን እንቆቅልሽህን አልነገርኸኝምና” አለችው። እርሱም፥ “እነሆ፥ ለአባቴና ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ለአንቺ እነግርሻለሁን?” አላት።
ሰባቱንም የበዓል ቀን አለቀሰችበት፤ እርስዋም ነዝንዛዋለችና በሰባተኛው ቀን ነገራት። ለሕዝብዋም ልጆች ነገረቻቸው።
ደሊላም፥ “ ‘አንተ እወድድሻለሁ’ እንዴት ትለኛለህ? ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም፤ ስታታልለኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኀይልህም በምን እንደ ሆነ አልነገርኸኝም” አለችው።
እርሱም፥ “ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር ናዝራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አልነካኝም፤ የራሴንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነሣል፤ እደክማለሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆናለሁ” ብሎ የልቡን ሁሉ ነገራት።