መሳፍንት 14:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወስዶም በላ፤ እየበላም ሄደ፤ ወደ አባቱና ወደ እናቱም ደረሰ፤ ሰጣቸውም፤ እነርሱም በሉ፤ ማሩንም ከአንበሳው አፍ ውስጥ እንዳወጣው አልነገራቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእጁ ወስዶም መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ከወላጆቹም ጋራ እንደ ተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነርሱም በሉ። ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን መሆኑን አልነገራቸውም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእጁ ወስዶም መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ከወላጆቹም ጋር እንደተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነርሱም በሉ። ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን መሆኑን አልነገራቸውም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማሩም ጥቂት በእጁ ቈርጦ እየበላ መንገዱን ቀጠለ፤ ወደ አባቱና ወደ እናቱ ቀርቦ ከያዘው ማር. ሰጥቶአቸው በሉ፤ ነገር ግን ሶምሶን ያንን ማር. ያገኘው ከሞተው አንበሳ በድን ውስጥ መሆኑን አልነገራቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእጁም ወስዶ መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፥ ወደ አባቱና ወደ እናቱ መጣ፥ ማሩንም ሰጣቸው፥ እነርሱም በሉ፥ ማሩንም ከአንበሳው ሬሳ ውስጥ እንደ ወሰደ አልነገራቸውም። |
ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ሊያገባት ተመለሰ፤ የአንበሳውንም ሬሳ ያይ ዘንድ ከመንገድ ፈቀቅ አለ፤ እነሆም፥ በአንበሳው አፍ ውስጥ ንብ ሰፍሮበት ነበር፤ ማርም ነበረበት።
በነጋም ጊዜ፥ የሳኦል ልጅ ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ በዚያ በኩል ወዳለው ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር እንለፍ” አለው፤ ለአባቱም አልነገረውም።