የእስራኤል ልጆች ከግብፅ በወጡበት በመጀመሪያው ዘመን እንዲህ ሆነ። በሦስተኛው ወር፥ ያ ወር በባተ በዐሥራ ስድስተኛው ቀን፥ እግዚአብሔር፥ “ከእኔ ዘንድ ወደዚህ ተራራ ውጣ፤ በጻፍኸውም መጠን ልብ ታስደርጋቸው ዘንድ ሕጉና ሥርዐቱ የተጻፉባቸውን ሁለቱን የዕንቍ ጽላት እሰጥሀለሁ” ብሎ ለሙሴ ተናገረ።