La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 9:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ጉባኤ ወደ ጌል​ገላ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥ​ተ​ናል፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ” አሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ኢያሱንና የእስራኤልን ሰዎች፣ “የመጣነው ከሩቅ አገር ነው፤ ከእኛ ጋራ ቃል ኪዳን ግቡ” አሏቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ አሉ፦ “ከሩቅ አገር መጥተናል፤ እንግዲህ አሁን ከእኛ ጋር የቃል ኪዳን አድርጉ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህን ሁሉ ካደረጉ በኋላ በጌልገላ ወደሚገኘው ሰፈር ሄደው ኢያሱንና እስራኤላውያንን፦ “እኛ የመጣነው ከሩቅ አገር ነው፤ የመጣነውም ከእናንተ ጋር የቃል ኪዳን ውል ለማድረግ ነው” አሉአቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሰዎች፦ ከሩቅ አገር መጥተናል፥ አሁንም ከእኛ ጋር ኪዳን አድርጉ አሉ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 9:6
9 Referencias Cruzadas  

“ከሕ​ዝ​ብ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ያል​ሆነ እን​ግዳ ስለ ስምህ ከሩቅ ሀገር ቢመጣ፥


ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያ​ስም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጥቶ፥ “እነ​ዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወ​ዴ​ትስ ወደ አንተ መጡ?” አለው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ከሩቅ ሀገር ከባ​ቢ​ሎን ወደ እኔ መጡ” አለው።


ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ ሰፈሩ ወደ ጌል​ገላ ተመ​ለሱ።


የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ ጌል​ገላ ልከው፥ “ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ለመ​ር​ዳት እጅ​ህን አት​መ​ልስ፤ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር የሚ​ኖሩ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በ​ው​ብ​ና​ልና ፈጥ​ነህ ወደ እኛ ውጣ፤ አድ​ነ​ንም፤ ርዳ​ንም፤” አሉት።


ሕዝ​ቡም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወጡ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም በም​ሥ​ራቅ በኩል በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ፤ ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ ምዕ​ራብ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ።


በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም ያደ​ረ​ጉት ጫማ ያረ​ጀና ማዘ​ቢ​ያው የተ​በ​ጣ​ጠሰ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ውም በላ​ያ​ቸው ያረጀ ነበረ፤ ለስ​ን​ቅም የያ​ዙት እን​ጀራ ሁሉ የደ​ረቀ፥ የሻ​ገ​ተና የተ​በ​ላሸ ነበረ።


እነ​ር​ሱም አሉት፥ “በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪ​ያ​ዎ​ችህ መጥ​ተ​ናል፤ ዝና​ው​ንም፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥