La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 9:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አለ​ቆ​ቹም ሁሉ ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምለ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ ስለ​ዚ​ህም እን​ነ​ካ​ቸው ዘንድ ምንም አን​ች​ልም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ስለማልንላቸው፣ አሁን ጕዳት ልናደርስባቸው አንችልም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አለቆቹም ሁሉ ለማኅበሩ ሁሉ እንዲህ አሉአቸው፦ “በእስራኤል አምላክ በጌታ ምለንላቸዋል፤ ስለዚህም እንነካቸው ዘንድ አይገባንም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መሪዎቹ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ገብተንላቸዋል፤ ስለዚህም አሁን ጒዳት ልናደርስባቸው አይገባም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አለቆቹም ሁሉ ለማኅበሩ ሁሉ፦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ምለንላቸዋል፥ ስለዚህም እንነካቸው ዘንድ አይገባንም።

Ver Capítulo



ኢያሱ 9:19
5 Referencias Cruzadas  

ልጄ ሆይ፥ የን​ጉ​ሥን አፍ ጠብቅ፤ ለመ​ሐላ ቃልም አት​ቸ​ኩል።


በሁ​ሉም ከን​ቱ​ነት አለ፥ የጻ​ድ​ቁና የበ​ደ​ለ​ኛው፥ የመ​ል​ካ​ሙና የክ​ፉው፥ የን​ጹ​ሑና የር​ኩሱ፥ መሥ​ዋ​ዕ​ትን የሚ​ሠ​ዋ​ውና የማ​ይ​ሠ​ዋው፥ የመ​ል​ካ​ሙና እን​ዲሁ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው፥ የመ​ሐ​ላ​ኛ​ውና እን​ዲሁ መሐ​ላን የሚ​ፈ​ራው ድርሻ አንድ ነው።


ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብሎ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት፤ በጽ​ድ​ቅም ቢምል፥ አሕ​ዛብ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።


የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ማሉ​ላ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አል​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውም። ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በአ​ለ​ቆቹ ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ።


ስለ​ማ​ል​ን​ላ​ቸው መሐላ ጥፋት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብን ይህን አና​ድ​ር​ግ​ባ​ቸው፤ በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ተ​ዋ​ቸው፤ እን​ግ​ዛ​ቸ​ውም” አሉ​አ​ቸው።