አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፤ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነሥቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ፤ በሦስተኛውም ቀን ደረሰ።
ኢያሱ 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፤ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው ሰበሰባቸው፤ በይሁዳም ነገድ ላይ ምልክት ታየ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት ኢያሱ ማልዶ ተነሣ፤ እስራኤልንም በየነገድ በየነገዳቸው ሆነው እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከዚያም የይሁዳ ነገድ ተለየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው አቀረበ፤ የይሁዳም ነገድ ተለየ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱም ማለዳ ኢያሱ እስራኤላውያንን በየነገዳቸው አምጥቶ አቀረባቸው፤ ከዚያም የይሁዳ ነገድ ለብቻው ተለየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው አቀረበ፥ የይሁዳም ነገድ ተለየ፥ |
አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፤ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነሥቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ፤ በሦስተኛውም ቀን ደረሰ።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
ምልክት የታየበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና፥ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።”