ኢያሱ 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእስራኤል ልጆች የታወቁትን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ የሾማቸውን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእስራኤል ልጆች የሾማቸውን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም የመረጣቸውን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእስራኤል ልጆች ያዘጋጃቸውን አሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ። |
በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ቀላል ድንጋዮችን እንዲያነሡ እዘዛቸው፤ ከእናንተም ጋር ውሰዱአቸው፤ ከዚያም ሌሊት በምታድሩበት ቦታ በየነገዳችሁ ጠብቋቸው።”
ኢያሱም አላቸው፥ “በእኔና በእግዚአብሔር ፊት ወደ ዮርዳኖስ መካከል ዕለፉ፤ እያንዳንዱ ሰው በዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ቍጥር በትከሻው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም።