ኢያሱ 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም፥ “የሚከተሉአችሁ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፤ የሚከተሉአችሁም እስከሚመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፤ በኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ” አለቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “የሚከታተሏችሁ ሰዎች እንዳያገኟችሁ ወደ ኰረብቶቹ ሂዱ፤ እነርሱ እስኪመለሱም ድረስ ሦስት ቀን በዚያ ተሸሸጉ፤ ከዚያ በኋላ መንገዳችሁን ትቀጥላላችሁ” አለቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም እንዲህ አለቻቸው፦ “አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፤ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፤ ከዚያም በኋላ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም ስትል መከረቻቸው፤ “ወደ ኮረብታማው አገር ሂዱ፤ ይህ ካልሆነ ግን የንጉሡ መልእክተኞች ሊያገኙአችሁ ይችላሉ፤ በዚያም እነርሱ እስኪመለሱ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ተደብቃችሁ ቈዩ፤ ከዚያን በኋላ ጒዞአችሁን መቀጠል ትችላላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም፦ አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፥ ኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለቻቸው። |
እነርሱም ወጥተው ወደ ተራራው ሄዱ፤ የሚከተሉአቸውና የሚፈልጉአቸውም እስኪመለሱ ሦስት ቀን በዚያ ተቀመጡ፤ በመንገዱም አላገኙአቸውም።
ዳዊትም በምድረ በዳ በጠባቡ በማሴሬም ይኖር ነበር፥ በአውክሞዲስ ውስጥም በዚፍ ተራራ ምድረ በዳ ተቀመጠ፤ ሳኦልም ሁልጊዜ ይፈልገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን በእጁ አሳልፎ አልሰጠውም።