ከዚያም ድንበራቸው ወደ ቤተ ገለዓም ይወጣል፤ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል ያልፋል፤ ድንበራቸውም ወደ ሮቤል ልጅ ወደ ሊቶን ቢዮን ይወጣል፤
ኢያሱ 18:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤተሳሚስም ምንጭ ያልፋል፤ በኢታሚም አቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ኬልዩት ይገባል፤ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቤዎን ድንጋይ ይወርዳል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ወደ ሰሜን ይታጠፍና በዓይንሳሚስ በኩል አድርጎ እስከ ጌሊሎት ይዘልቃል፤ ከዚያም በአዱሚም መተላለፊያ ትይዩ እስካለው እስከ ሮቤል ልጅ እስከ ቦሀን ድንጋይ ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሰሜንም ታጥፎ በቤትሳሚስ ምንጭ ላይ ወጣ፥ በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ጌሊሎት ደረሰ፤ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወረደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ወደ ሰሜን በመታጠፍ ወደ ዔንሺሜሽ አቅጣጫ ይሄዳል፤ ከዚያም ወደ ገሊሎት ይሄዳል፤ እርሱም ከአዱሚም ዐቀበት ትይዩ ነው፤ እንዲሁም የሮቤል ልጅ ወደ ሆነው ወደ ቦሄን ድንጋይ ይወርዳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሰሜንም አለፈ በቤትሳሚስ ምንጭ ላይ ወጣ፥ በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ጌሊሎት ደረሰ፥ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወረደ፥ |
ከዚያም ድንበራቸው ወደ ቤተ ገለዓም ይወጣል፤ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል ያልፋል፤ ድንበራቸውም ወደ ሮቤል ልጅ ወደ ሊቶን ቢዮን ይወጣል፤
ድንበሩም በአኮር ሸለቆ አራተኛ ክፍል ላይ ይወጣል፤ በአዱሚን ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ይወርዳል፤ ድንበሩም ወደ ፀሐይ ምንጭ ውኃ ያልፋል፤ መውጫውም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ነበረ፤