ዮሐንስ 9:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈሪሳውያንም ከእርሱ ጋር የነበሩት ይህን ሲናገር ሰምተው፥ “እኛ ደግሞ ዕዉሮች ነን?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ጋራ ከነበሩት ፈሪሳውያን አንዳንዶቹ ይህን ሰምተው፣ “ምን ማለትህ ነው? ታዲያ እኛም ዕውሮች መሆናችን ነው?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ ጋር ከነበሩት ፈሪሳውያንም መሀል ይህንን ሰምተው “እኛ ደግሞ ዕውሮች ነንን?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በኢየሱስ አጠገብ የነበሩ ፈሪሳውያን ይህን ሰምተው “ታዲያ፥ እኛም ዕውሮች መሆናችን ነውን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፈሪሳውያንም ከእርሱ ጋር የነበሩት ይህን ሰምተው፦ “እኛ ደግሞ ዕውሮች ነንን?” አሉት። |
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ዕዉሮችስ ብትሆኑ ኀጢኣት ባልሆነባችሁም ነበር፤ አሁን ግን እናያለን ትላላችሁ፤ አታዩምም፤ ስለዚህም ኀጢኣታችሁ ጸንቶ ይኖራል” አላቸው።
‘ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ፤ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም፤’ የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥