ዮሐንስ 9:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም፥ “የምታየው፥ ከአንተ ጋርም የሚነጋገረው እርሱ ነው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “አይተኸዋል፤ አሁንም ከአንተ ጋራ የሚነጋገረው እርሱ ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም “አይተኸዋል፤ ከአንተ ጋርም የሚናገረው እርሱ ነው፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ “ከዚህ በፊት አይተኸዋል፤ አሁንም የሚያነጋግርህ እርሱ ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ “አይተኸዋልም ከአንተ ጋርም የሚናገረው እርሱ ነው” አለው። |
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድድ ግን ትምህርቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የምናገረውም ከራሴ እንዳይደለ እርሱ ያውቃል።