ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
ዮሐንስ 7:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን አውቀዋለሁ፤ እኔ ከእርሱ ነኝና፥ እርሱም ልኮኛልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ግን ከርሱ ዘንድ ስለ ሆንሁ፣ እርሱም ስለ ላከኝ ዐውቀዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ነኝ፤ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ፤” ብሎ ጮኸ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ስለ መጣሁና እርሱ ስለ ላከኝ ዐውቀዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ነኝ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ” ብሎ ጮኸ። |
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
ጌታችን ኢየሱስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ባወቀ ጊዜ፥
እናንተም አታውቁትም፤ እኔ ግን ኣውቀዋለሁ፤ አላውቀውም ብልም እንደ እናንተ ሐሰተኛ እሆናለሁ፤ እኔ አውቀዋለሁ ቃሉንም እጠብቃለሁ።