ዮሐንስ 13:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ደቀ መዝሙር በጌታችን ኢየሱስ አጠገብ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታ ሆይ፥ እርሱ ማነው?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ፣ “ጌታ ሆይ፤ ማን ይሆን?” ብሎ ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ “ጌታ ሆይ! ማን ነው?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እርሱ አንገቱን ወደ ኢየሱስ አስጠጋና “ጌታ ሆይ! አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም በኢየሱስ ደረት እንዲህ ተጠግቶ፦ “ጌታ ሆይ፥ ማን ነው?” አለው። |
ጴጥሮስም መለስ ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ይወደው የነበረውን ያን ደቀ መዝሙር ሲከተለው አየ፤ እርሱም ራት ሲበሉ በጌታችን በኢየሱስ አጠገብ የነበረውና “ጌታ ሆይ፥ አሳልፎ የሚሰጥህ ማነው?” ያለው ነው።