ዮሐንስ 10:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ግን አታምኑኝም፤ እንደ ነገርኋችሁ ከበጎች ውስጥ አይደላችሁምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ግን ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን ከበጎቼ መንጋ ስላልሆናችሁ አታምኑም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም። |
ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ ስለዚህ እናንተ አትሰሙኝም፤ ከእግዚአብሔር አይደላችሁምና።”
እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን።