ኢዮብ 42:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጀመሪያይቱን ስም ዕለት፥ የሁለተኛይቱንም ስም ቃስያ፥ የሦስተኛይቱንም ስም አማልትያስቂራስ ብሎ ሰየማቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመጀመሪያዋን ይሚማ፣ ሁለተኛዋን ቃሥያ፣ ሦስተኛዋንም አማልቶያስ ቂራስ ብሎ ሰየማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጀመሪያይቱንም ይሚማ፥ ሁለተኛይቱንም ቃስያ፥ ሦስተኛይቱንም ቄሬንህፉክ ብሎ ሰየማቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሴቶች ልጆቹ የመጀመሪያዋን ይሚማ፥ ሁለተኛዋን ቀጺዐ ሦስተኛዋን ቄሬንሀፉክ ብሎ ሰየማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመጀመሪያይቱንም ስም ይሚማ፥ የሁለተኛይቱንም ስም ቃስያ፥ የሦስተኛይቱንም ስም አማልቶያስ ቂራስ ብሎ ሰየማቸው። |
ከሰማይ በታች እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች ያሉ የተዋቡ ሴቶች በሀገሩ ሁሉ አልተገኙም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት ሰጣቸው።