ምድርም ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማይ መሠረቶችም ተነቃነቁ፤ ተንቀጠቀጡም፤ እግዚአብሔር ተቈጥቶአልና።
ኢዮብ 26:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ይደነግጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰማይ ምሰሶዎች ይንቀጠቀጣሉ፤ በተግሣጹም ይደነግጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ይደነግጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በሚገሥጻቸው ጊዜ፥ የሰማይ አዕማድ በድንጋጤ ይናወጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ይደነግጣሉ። |
ምድርም ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማይ መሠረቶችም ተነቃነቁ፤ ተንቀጠቀጡም፤ እግዚአብሔር ተቈጥቶአልና።
የእግዚአብሔር ሕግ ንጹሕ ነው፤ ነፍስንም ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትንም ጠቢባን ያደርጋል።
የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፤ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።