ኢዮብ 12:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀይልና ብርታት በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ ዕውቀትና ማስተዋልም ለእርሱ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርታትና ጥበብ ማድረግ በርሱ ዘንድ ይገኛል፤ አታላዩም ተታላዩም በርሱ እጅ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፥ የሚስተውና የሚያስተው የእርሱ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ብርቱና ድል አድራጊ ነው፤ የሚታለልም ሆነ የሚያታልል ሁለቱም በእርሱ ሥልጣን ሥር ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፥ የሚስተውና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው። |
እርሱ ግን ጠቢብ ነው፤ ክፉንም ነገር በላያቸው ያመጣል፤ ቃሉንም አይመልስም፤ በክፉዎችም ሰዎች ቤት ላይ በከንቱ ተስፋቸውም ላይ ይነሣል።
ነቢዩም ቢታለል፥ ቃልንም ቢናገር፥ ያን ነቢይ ያታለልሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ እጄንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከሕዝቤም ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ።