ኤርምያስ 23:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለነቢዩ፥ “እግዚአብሔር ምን መለሰልህ እግዚአብሔርስ የተናገረው ምንድን ነው?” በሉ ምን ተናገረ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ለነቢዩ፣ ‘እግዚአብሔር ምን መልስ ሰጠህ?’ ወይም፣ ‘እግዚአብሔር ምን ተናገረህ?’ ትለዋለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለነቢዩ እንዲህ ትለዋለህ፦ ‘ጌታ ምን መለሰልህ?’ ‘ጌታስ የተናገረው ምንድነው?’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም ኤርምያስ ሆይ፥ ነቢዩን ‘እግዚአብሔር ምን መልስ ሰጠህ? ምንስ ተናገረህ’ ብለህ ጠይቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለነቢዩ፦ እግዚአብሔር ምን መለሰልህ? እግዚአብሔርስ የተናገረው ምንድር ነው? ትላለህ። |
ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆንበታልና የእግዚአብሔር ሸክም ብላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ አትጥሩ፤ የሠራዊትን ጌታ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን የሕያውን አምላክ ቃል ለውጣችኋልና።
ነገር ግን፥ “የእግዚአብሔር ሸክም” ብትሉ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እኔ፦ የእግዚአብሔር ሸክም አትበሉ ብዬ ልኬባችኋለሁና፥ እናንተም ይህን ቃል፦ የእግዚአብሔር ሸክም ብላችኋልና፥