ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
ዘፍጥረት 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኔም እነሆ፥ ቃል ኪዳኔን ከእናንተ ጋር፥ ከእናንተም በኋላ ከዘራችሁ ጋር አጸናለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ ከእናንተና ከእናንተ በኋላ ከሚመጣው ዘራችሁ ጋራ ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ እኔም ቃል ኪዳኔን ከእናንተ ጋር፥ ከእናንተም በኋላ ከዘራችሁ ጋር እመሠርታለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ፥ ከእናንተና ከዘራችሁ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተና በኍላ ከሚመጣው ከዘራችሁ ጋር አቆማለሁ፤ |
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
ቃል ኪዳኔንም ከአንተ ጋር አጸናለሁ፤ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን፥ የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ።
ከእናንተ ጋር ላሉትም፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፥ ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት ለወፎች፥ ለእንስሳትም፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ፥ ለማንኛውም ለምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል።
ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ፤ ሥጋ ያለውም ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም።”
እግዚአብሔርም ኖኅን፥ “በእኔና በምድር ላይ በሚኖር፥ ሥጋ ባለው ሁሉ መካከል ያጸናሁት የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው” አለው።
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በወራታቸው እንዳይሆኑ የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፥