ዘፍጥረት 9:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቴ በደመናው ትታያለች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናን በምድር ላይ በጋረድሁና ቀስቴም በደመና ላይ በሚታይበት ጊዜ ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር በደመና በምትሸፈንበት ቀስቲቱም በደመናው በምትታይበት ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰማይን በደመና በምሸፍንበትና ቀስትም በደመና ላይ በሚታይበት ጊዜ ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቲቱ በደመናው ትታያለች፤ |
በእኔና በእናንተ መካከል፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ሥጋ ሁሉ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ሥጋ ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ ዳግመኛ የጥፋት ውኃን አላመጣም።