ዘፍጥረት 41:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ ሥጋቸው የወፈረ፥ መልካቸውም ያማረ ሰባት ላሞች ወጡ፤ በወንዙ ዳር በመስኩም ይሰማሩ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋቸው የወፈረና መልካቸው ያማረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ሲበሉ አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋቸው የወፈረና መልካቸው ያማረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ሲበሉ አየሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባት የወፈሩና የሰቡ ላሞች ከወንዙ ወጥተው ሣር ሲበሉ አየሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም ሥጋቸውም የወፈረ መልካቸውም ያማረ ሰባት ላሞች ወጡ በመስኩም ይስማሩ ነበር። |
ከእነርሱም በኋላ እነሆ፥ የደከሙ፥ መልካቸውም እጅግ የከፋ፥ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ፤ በግብፅም ምድር ሁሉ እንደ እነርሱ መልከ ክፉ ከቶ አላየሁም፤
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፥ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳን ምርኮ ለበጎነት እመለከተዋለሁ።
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፥ “ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉው በለስ፥ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፤ አለቆቹንም፥ በዚች ሀገር የሚቀሩትንም የኢየሩሳሌምን ቅሬታ፥ በግብጽም ሀገር የሚቀመጡትን እንዲሁ አደርጋቸዋለሁ።