ዘፍጥረት 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ቃየልን አለው፥ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” ቃየልም አለ፥ “አላውቅም፤ በውኑ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ እግዚአብሔር ቃየንን፣ “ወንድምህ አቤል የት ነው?” አለው። ቃየንም፣ “አላውቅም፤ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ቃየንን፥ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” አለው። እርሱም፥ “አላውቅም፥ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ?” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ቃየልን “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” ሲል ጠየቀው፤ ቃየልም “የት እንዳለ አላውቅም፤ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፤ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ፤ አላውቅም የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም፤ |
ብዙ ኅብር ያለበትን ቀሚሱንም ላኩ፤ ወደ አባታቸውም አገቡት፤ እንዲህም አሉት፥ “ይህን ልብስ አገኘን፤ ይህ የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው?”
እናንተስ ከአባታችሁ ከሰይጣን ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፈቃድ ልታደርጉ ትወዳላችሁ፤ እርሱ ከጥንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእውነትም አይቆምም፤ በእርሱ ዘንድ እውነት የለምና፤ ሐሰትንም በሚናገርበት ጊዜ ከራሱ አንቅቶ ይናገራል፤ ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰትም አባት ነውና።