La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 39:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የግ​ዞት ቤቱ ጠባ​ቂ​ዎች አለ​ቃም በግ​ዞት ቤት የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ምንም አያ​ው​ቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮ​ሴፍ ትቶ​ለት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረና፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ያቀ​ና​ለት ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋራ ሆኖ ሥራውን ሁሉ ያሳካለት ስለ ነበር፣ የወህኒ ቤት አዛዡ በዮሴፍ ኀላፊነት ሥር ስላለው ስለ ማንኛውም ጕዳይ ሐሳብ አይገባውም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ ሥራውን ሁሉ ያሳካለት ስለ ነበር፥ የወህኒ ቤት አዛዡ በዮሴፍ ኀላፊነት ሥር ስላለው ስለማንኛውም ጉዳይ ሐሳብ አይገባውም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ የሚያደርገው ነገር ሁሉ እንዲቃናለት ስላደረገ የእስር ቤቱ አዛዥ በዮሴፍ ቊጥጥር ሥር በነበረው ነገር ምንም ሐሳብ አልነበረበትም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የግዞት ቤቱን አለቃ በእጁ ያለውን ነገር ከቶ አላሰበም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር ያቀናለት ነበር።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 39:23
10 Referencias Cruzadas  

ዮሴ​ፍ​ንም ወሰ​ደው፤ የን​ጉሡ እስ​ረ​ኞች ወደ​ሚ​ታ​ሰ​ሩ​በት ስፍራ ወደ ግዞት ቤትም አገ​ባው፤ ከዚ​ያም በግ​ዞት ነበረ።


እር​ሱም እንቢ አለ፤ ለጌ​ታ​ውም ሚስት እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ ጌታዬ በቤቱ ያለ​ውን ሁሉ ለእኔ በእጄ አስ​ረ​ክ​ቦ​ኛል፤ በቤቱ ያለ​ው​ንም ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም፤


እር​ሱም በውኃ ፈሳ​ሾች ዳር እንደ ተተ​ከ​ለች፥ ፍሬ​ዋን በየ​ጊ​ዜዋ እን​ደ​ም​ት​ሰጥ፥ ቅጠ​ል​ዋም እን​ደ​ማ​ይ​ረ​ግፍ ዛፍ ይሆ​ናል፤ የሚ​ሠ​ራ​ውም ሁሉ ይከ​ና​ወ​ን​ለ​ታል።


በውኃ ውስጥ ባለ​ፍህ ጊዜ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ ወን​ዞ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​ህም፤ በእ​ሳ​ትም ውስጥ በሄ​ድህ ጊዜ አት​ቃ​ጠ​ልም፤ ነበ​ል​ባ​ሉም አይ​ፈ​ጅ​ህም።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ው​ነት ቤትህ፥ የአ​ባ​ት​ህም ቤት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊቴ እን​ዲ​ኖር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያከ​በ​ሩ​ኝን አከ​ብ​ራ​ለ​ሁና፥ የና​ቁ​ኝም ይና​ቃ​ሉና ይህ አይ​ሆ​ን​ል​ኝም።