ዘፍጥረት 39:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ልብሱን ትቶ ወደ ውጭ እንደ ሸሸ በአየች ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ መውጣቱን ባየች ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ መውጣቱን ባየች ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ልብሱን በእጅዋ ላይ ትቶ ከቤት ሸሽቶ መውጣቱን በተመለከተች ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆን ልብሱን ትቶ ወደ ውጭ እንደ ሸሸ ባየች ጊዜ |
የቤቷን ሰዎች ወደ እርስዋ ጠርታ እንዲህ ብላ ነገረቻቸው፥ “እዩ፤ ይህ ዕብራዊ ባርያ በእኛ እንዲሣለቅ አመጣብን፤ እርሱ ወደ እኔ ገብቶ ከእኔ ጋር ተኚ አለኝ፤ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ፤