ስለዚህም በፊትህ ያለውን ደመወዜን ለመመልከት በመጣህ ጊዜ ወደፊት ጻድቅነቴን ይመሰክርልኛል፤ ከፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ የሌለበት፥ ከበግ ጠቦቶችም ጥቁር ያልሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰረቀ ይቈጠርብኝ።”
ዘፍጥረት 30:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም፥ “እነሆ እንደ ቃልህ ይሁን” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባም፣ “ዕሺ፣ ይሁን፤ ባልኸው ተስማምቻለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም፦ “እነሆ እንደ ቃልህ ይሁን” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባም “እሺ አንተ ባልከው እስማማለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም፦ እነሆ እንደ ቃልህ ይሁን አለ። |
ስለዚህም በፊትህ ያለውን ደመወዜን ለመመልከት በመጣህ ጊዜ ወደፊት ጻድቅነቴን ይመሰክርልኛል፤ ከፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ የሌለበት፥ ከበግ ጠቦቶችም ጥቁር ያልሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰረቀ ይቈጠርብኝ።”
በዚያም ቀን ከተባቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹ ፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ፥ ከበጎቹም መካከል ጥቁሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው።
ሁላችሁም በቋንቋ ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ይልቁንም ትንቢት ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ሳይተረጕም በቋንቋ ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር እጅግ ይበልጣልና፤ ቢተረጕም ግን ማኅበሩን ያንጻል።
ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ እግዚአብሔር እንደ አደለው ጸጋ ይኑር፤ ግብሩ እንዲህ የሆነ አለና፤ ግብሩ ሌላ የሆነም አለና።