ሮቤል ስንዴ በሚታጨድበት ወራት ወጣ፤ በእርሻም እንኮይ አገኘ፥ ለእናቱ ለልያም አመጣላት። ራሔልም ልያን፥ “የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።
ዘፍጥረት 30:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ሲመሽ ከዱር ገባ፤ ልያም ልትቀበለው ወጣች፤ እንዲህም አለችው፥ “እኔ ዘንድ ታድራለህ፤ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተስማምቼሃለሁና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ምሽት ያዕቆብ ከዕርሻ ሲመለስ፣ ልያ ወጥታ ተቀበለችውና፣ “በልጄ እንኮይ ስለ ተከራየሁህ የዛሬው ዐዳርህ ከእኔ ጋራ ነው” አለችው፤ ያዕቆብም በዚያች ሌሊት ከርሷ ጋራ ዐደረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ሲመሽ ከዱር ገባ፥ ልያም ልትቀበለው ወጣች እንዲህም አለችው፦ “ወደ እኔ ትገባለህ፥ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተከራይቼሃለሁና።” በዚያችም ሌሊት ከእርሷ ጋር ተኛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ምሽት ያዕቆብ ከዱር ሲመለስ፥ ልያ ከቤት ወደ እርሱ ወጥታ “በልጄ እንኮይ ስለ ገዛሁህ ዛሬ ሌሊት የምታድረው ከእኔ ጋር ነው” አለችው፤ ስለዚህ በዚያን ሌሊት ከእርስዋ ጋር ዐደረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብ ሲመሽ ከዱር ገባ፥ ልያም ልትቀበለው ወጣች እንዲህም አለችው፦ ወደ እኔ ትገባለህ፤ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተከራይቼሃለሁና። በዚያችም ሌሊት ከእርስዋ ጋር ተኛ። |
ሮቤል ስንዴ በሚታጨድበት ወራት ወጣ፤ በእርሻም እንኮይ አገኘ፥ ለእናቱ ለልያም አመጣላት። ራሔልም ልያን፥ “የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።
ልያም፥ “ባሌን መውሰድሽ አይበቃሽምን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይደር” አለች፤ ሰጠቻትም።
በዚያችም ሌሊት ከእርስዋ ጋር አደረ። እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፤ ፀነሰችም፤ አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች።