በአብራምና በሎጥ መንጎች ጠባቆች መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።
ዘፍጥረት 21:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክም አለ፥ “ይህን ነገር ማን እንዳደረገው አላወቅሁም፤ አንተም ደግሞ ምንም አልነገርኸኝም፤ እኔም ከዛሬ በቀር አልሰማሁም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢሜሌክም፣ “መቼም ይህን ድርጊት ማን እንደ ፈጸመ በበኩሌ አላውቅም፤ አንተም አልነገርኸኝም፤ ነገሩንም ገና አሁን መስማቴ ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቢሜሌክም አለ፦ “ይህን ነገር ያደረገውን አላወቅሁም፥ አንተም ደግሞ ምንም አልነገርኸኝም፥ እኔም ከዛሬ በቀር አልሰማሁም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሜሌክም “ይህን ያደረገው ማን እንደ ሆነ አላውቅም፤ አንተም አልነገርከኝም፤ ይህን ነገር ገና ዛሬ መስማቴ ነው” አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢሜሌክም አለ፦ ይህን ነገር ያደረገውን አላውቅሁም፤ አንተም ደግሞ ምንም አልነገርኸኝም፥ እኔም ከዛሬ በቀር አልሰማሁም። |
በአብራምና በሎጥ መንጎች ጠባቆች መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።