እግዚአብሔርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በየዘሩ የሚዘራውንና የሚበቅለውን፥ በምድር ሁሉ ላይ የምትዘሩትን የእህል ፍሬ፥ ዘሩ በውስጡ ያለውን ቡቃያ፥ በየፍሬውም የሚዘራውን ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ።
ዘፍጥረት 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም አዳምን እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ በማለት አዘዘው፤ “በአትክልት ስፍራው ውስጥ ከሚገኝ ከማንኛውም ዛፍ ፍሬ ትበላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ጌታ እግዚአብሔር ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ ብላ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “በአትክልቱ ቦታ ከሚገኙት ዛፎች ሁሉ ፍሬ ልትበላ ትችላለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፤ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ |
እግዚአብሔርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በየዘሩ የሚዘራውንና የሚበቅለውን፥ በምድር ሁሉ ላይ የምትዘሩትን የእህል ፍሬ፥ ዘሩ በውስጡ ያለውን ቡቃያ፥ በየፍሬውም የሚዘራውን ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ።
እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያሳየውንና የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።