ምድርም በየዘሩ፥ በየወገኑና በየመልኩ የሚዘራ ቡቃያን፥ በምድር ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ዘፍጥረት 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም “ምድር በየዘሩ፥ በየወገኑና በየመልኩ ዘር የሚሰጥ ቡቃያን፥ በምድርም ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ “ምድር ዕፀዋትንም፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በምድር ላይ ዘር ያዘሉ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም፦ “ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል” አለ፥ እንዲሁም ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር አትክልትን፥ የእህል አዝርዕትን፥ ፍሬ የሚያፈሩ የፍሬ ዛፎችንና ተክሎችን በየዐይነቱ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፤ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ። |
ምድርም በየዘሩ፥ በየወገኑና በየመልኩ የሚዘራ ቡቃያን፥ በምድር ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
እግዚአብሔርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በየዘሩ የሚዘራውንና የሚበቅለውን፥ በምድር ሁሉ ላይ የምትዘሩትን የእህል ፍሬ፥ ዘሩ በውስጡ ያለውን ቡቃያ፥ በየፍሬውም የሚዘራውን ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ።
የሜዳ ቍጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ከመኖሩ በፊት፥ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ከመብቀሉ በፊት፥ አዳምም ከመፈጠሩ በፊት፥ እግዚአብሔር አምላክ በምድር ላይ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም።
እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያሳየውንና የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
ምድርም ቡቃያውን እንደምታወጣ፥ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፥ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ደስታን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል።
በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ፥ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ፥ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።
እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?
ምድርም በእርስዋ የሚወርደውን ዝናም ከጠጣች፥ ያንጊዜ ስለ እርሱ ያረሱላትን መላካም ቡቃያ ታበቅላለች፤ ከእግዚአብሔር ዘንድም በረከትን ታገኛለች።