የእስራኤልም ልጆች አለቆች ዕለት ዕለት ከምትሠሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታጕድሉ ባሉአቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ።
ዘፀአት 5:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈርዖንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴንና አሮንን በፊታቸው ቆመው ተገናኙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፈርዖን ዘንድ እንደ ተመለሱ ሲጠብቋቸው የነበሩትን ሙሴንና አሮንን አግኝተው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፈርዖንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴንና አሮንን ቆመው አገኙአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንጉሡም ፊት እንደ ወጡ፥ እነርሱን በመጠባበቅ ላይ የነበሩትን ሙሴንና አሮንን አገኙአቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፈርዖንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴንና አሮንን በፊታቸው ቆመው ተገናኙአቸው። |
የእስራኤልም ልጆች አለቆች ዕለት ዕለት ከምትሠሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታጕድሉ ባሉአቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ።
እነርሱም፥ “በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድለንም ዘንድ ሰይፍን በእጁ ሰጥታችሁታልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም” አሉአቸው።