ዘፀአት 38:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰሜኑም ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎች፥ ከናስም የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎችንና ሃያ እግሮችን፥ ለምሰሶዎችም የብር ኵላቦችንና ዘንጎችን አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሜኑም ክፍል ቁመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር፤ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ የንሓስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰሜን በኩል መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቻቸው ሃያ የነሐስ እግሮቻቸውም ሃያ ነበሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሰሩ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰሜንም በኩል የአደባባዩ አሠራር እንደዚሁ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰሜኑም ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጆች፥ ከናስም የተሠራ ሀያ ምሰሶችንና ሀያ እግሮችን፥ ለምሰሶቹም የብር ኩላቦችንና ዘንጎችን አደረገ። |
ሃያውንም ምሰሶዎቻቸውንና ሃያውን እግሮቻቸውን ከናስ አደረገ፤ የምሰሶዎቹንም ኵላቦችና ዘንጎች ከብር አደረገ።
በምዕራብም ወገን አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎች፥ ዐሥሩንም ምሰሶዎች፥ ዐሥሩንም የናስ እግሮች፥ ለምሰሶዎቹም የብር ኵላቦችንና ዘንጎችን አደረገ።