መክብብ 8:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ዕውቀት በእርሱ ላይ ታላቅ ስለ ሆነ ለነገር ሁሉ ጊዜና ፍርድ አለውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው መከራ እጅግ ቢጫነውም፣ ለሁሉም ነገር ትክክለኛ ጊዜና ተገቢ አሠራር አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው መከራ በእርሱ ላይ እጅግ ስለ ሆነ ለነገር ሁሉ ጊዜና ፍርድ አለውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕይወት አስቸጋሪ ቢሆንም ለሁሉም ነገር ጊዜና ቦታ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው መከራ በእርሱ ላይ እጅግ ስለ ሆነ ለነገር ሁሉ ጊዜና ፍርድ አለውና። |
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
የሠራው ሥራ ሁሉ በጊዜው መልካም ነው፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘለዓለምነትን በልቡ ሰጠው።
እኔም በልቤ፥ “በዚያ ለነገር ሁሉና ለሥራ ሁሉ ጊዜ አለውና በጻድቁና በኀጢአተኛው ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል” አልሁ።
ባለቤቱ ተነሥቶ ደጁን ይዘጋልና፤ ያንጊዜ ከደጅ ቆመው፦ ‘አቤቱ፥ አቤቱ፥ ክፈትልን’ እያሉ በር ሊመቱ ይጀምራሉ፤ መልሶም፦ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም ይላቸዋል።