መክብብ 7:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርቃና እጅግ ጠልቃ ሳለች መርምሮ የሚያገኛት ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብ ምንም ይሁን ምን፣ እጅግ ጥልቅና ሩቅ ነው፤ ማንስ ሊደርስበት ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሆነው ነገር ራቀ፥ እጅግም ጠለቀ፥ መርምሮ የሚያገኘውስ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ የጠለቀና ከባድ ስለ ሆነ ጥበብን መርምሮ ማወቅ የሚችል ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሆነው ራቀ እጅግም ጠለቀ፥ መርምሮ የሚያገኘውስ ማን ነው? |
ከፀሓይም በታች የተደረገውን ሥራ መርምሮ ያገኝ ዘንድ ለሰው እንዳይቻለው የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ አየሁ። ሰውም ሊፈልግ እጅግ ቢደክም መርምሮ አያገኘውም፤ ደግሞም ጠቢብ ሰው፥ “ይህን ዐወቅሁ” ቢል እርሱ ያገኘው ዘንድ አይችልም።
የእግዚአብሔር ባለጠግነት፥ ጥበብና ዕውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ለመንገዱም ፍለጋ የለውም፤ ፍርዱንም የሚያውቀው የለም።
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።