ምሣሩ ከዛቢያው ቢወልቅ ሰውየው ፊቱን ወዲያና ወዲህ ይላል፤ ብዙ ኀይልም ያስፈልገዋል። ጥበብ ግን ለብርቱ ሰው ትርፉ ነው፤
መክብብ 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንጋይን የሚፈነቅል ይታመምበታል፥ ዕንጨትንም የሚፈልጥ ይጐዳበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንጋይ የሚፈነቅል ይጐዳበታል፤ ግንድንም የሚፈልጥ አደጋ ላይ መውደቁ አይቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንጋይን የሚፈነቅል ይታመምበታል፥ እንጨትንም የሚፈልጥ ይጐዳበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንጋይን የሚፈነቅል በፈነቀለው ድንጋይ ራሱ ይጐዳል፤ እንጨትን የሚፈልጥ በፈለጠው እንጨት ይቈስላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋይን የሚፈነቅል ይታመምበታል፥ እንጨትንም የሚፈልጥ ይጐዳበታል። |
ምሣሩ ከዛቢያው ቢወልቅ ሰውየው ፊቱን ወዲያና ወዲህ ይላል፤ ብዙ ኀይልም ያስፈልገዋል። ጥበብ ግን ለብርቱ ሰው ትርፉ ነው፤