መክብብ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቀኝ ይመለሳል፥ ወደ ሰሜንም ይዞራል፤ ነፋስ ዙሪያዉን ዙሮ ይሄዳል፥ ነፋስም በዙረቱ ይመለሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፤ ወደ ሰሜንም ይመለሳል፤ ዞሮ ዞሮ ይሄዳል፤ ዘወትርም ወደ ዑደቱ ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፋስ ወደ ደቡብ ይሄዳል፥ ወደ ሰሜንም ይዞራል፥ ዘወትር በዙረቱ ይዞራል፥ ነፋስም በዙረቱ ደግሞ ይመለሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፋስ ወደ ደቡብም፥ ወደ ሰሜንም ይነፍሳል፤ ዞሮ ዞሮም እንደገና ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፋስ ወደ ደቡብ ይሄዳል፥ ወደ ሰሜንም ይዞራል፥ ዘወትር በዙረቱ ይዞራል፥ ነፋስም በዙረቱ ደግሞ ይመለሳል። |
የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች፥ አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም።
እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፤ በባሕሩም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፤ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።
ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳልና፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከየት እንደሚመጣ ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የሚወለድ ሁሉ እንዲሁ ነው።”