ለሌዋውያንም ከተሞችን ትሰጣላችሁ፤ ከምትሰጡአቸውም ከተሞች ስድስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚሸሽባቸው የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ ከእነዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተሞችን ትሰጣላችሁ።
ዘዳግም 4:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትናንት፥ ከትናት በስቲያም ጠላቱ ያልሆነውን ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ ገዳዩ ይማፀንባቸው ዘንድ፥ ከእነዚህም ከተሞች በአንዲቱ ተማፅኖ በሕይወት ይኖር ዘንድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም የቈየ ጠላትነት ሳይኖር፣ በድንገት ባልንጀራውን የገደለ ማንኛውም ሰው ሸሽቶ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመሄድ ሕይወቱን ማትረፍ ይችል ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም ማድረጉ ትናንት ከትናንት በስቲያም ከዚህ ቀድሞ ጠላትነት ሳይኖረው፥ ባልንጀራውን ሳያውቅ የገደለ፥ ገዳዩ ይሸሽባቸው ዘንድ፥ ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት እንዲኖር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ማድረጉ ቀድሞ ጠላትነት ሳይኖረው ባለማወቅ ማንኛውንም ሰው የገደለ ሕይወቱን ለማትረፍ ወደዚያ ሄዶ ማምለጥ እንዲችል ነው፤ አምልጦም ከእነዚህ ከተማዎች ወደ አንዲቱ ከገባ ሕይወቱን ያድናል። |
ለሌዋውያንም ከተሞችን ትሰጣላችሁ፤ ከምትሰጡአቸውም ከተሞች ስድስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚሸሽባቸው የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ ከእነዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተሞችን ትሰጣላችሁ።
ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ባሶር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።