ሙሴም በዚያች ቀን ይህችን መዝሙር ጻፋት፤ ለእስራኤልም ልጆች አስተማራት፤ ሙሴም ገባ እርሱና የነዌ ልጅ ኢያሱም የዚህችን ሕግ ቃሎች ሁሉ በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ።
ዘዳግም 32:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ይህን ቃል ሁሉ ለእስራኤል ሁሉ ተናግሮ ፈጸመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለመላው እስራኤል ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴ እነዚህን ቃላት ሁሉ ለመላው እስራኤል አሰምቶ ከጨረሰ በኋላ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ እነዚህን ቃላት ሁሉ ለሕዝቡ አሰምቶ ከጨረሰ በኋላ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ይህን ቃል ሁሉ ለእስራኤል ሁሉ ተናግሮ ፈጸመ። |
ሙሴም በዚያች ቀን ይህችን መዝሙር ጻፋት፤ ለእስራኤልም ልጆች አስተማራት፤ ሙሴም ገባ እርሱና የነዌ ልጅ ኢያሱም የዚህችን ሕግ ቃሎች ሁሉ በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ።
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዝዙበት ዛሬ የምመሰክርላችሁን ቃል ሁሉ በልባችሁ አኑሩት።