ዘዳግም 20:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሐፍቱም ለሕዝቡ ነግረው በጨረሱ ጊዜ ከታላላቁ ሕዝብ መካከል የሠራዊት አለቆችን ይሹሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለቆቹ ለሰራዊቱ ተናግረው ሲያበቁ፣ አዛዦችን በሰራዊቱ ላይ ይሹሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቹ ለሠራዊቱ ተናግረው ሲያበቁ፥ አዛዦችን በሠራዊቱ ላይ ይሹሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጦር መሪዎቹ ለሠራዊቱ ይህን ተናግረው ከጨረሱ በኋላ ለእያንዳንዱ ክፍል አዛዦችን ይምረጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹም ለሕዝቡ ነግረው በጨረሱ ጊዜ በየጭፍራው በሕዝቡ ላይ የጦር አለቆችን ይሹሙ። |
ጸሐፍቱም ደግሞ ጨምረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድንጉጥ ሰው ቢሆን የወንድሞቹን ልብ እንደ እርሱ እንዳያስፈራ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ ብለው ለሕዝቡ ይናገሩ።