ጌታ ሆይ! በፍጹም ቸርነትህ ቍጣህንና መቅሠፍትህን ከከተማህ ከኢየሩሳሌምና ከተቀደሰው ተራራህ መልስ፤ ስለ ኀጢአታችንና ስለ አባቶቻችን በደል ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ላሉት ሁሉ መሰደቢያ ሆነዋልና።