እኔ ዳንኤልም የባሪ ክፍል በምትሆን በሱሳ ነበርሁ፤ ስመለከትም እነሆ ከምዕራብ ወገን አንድ አውራ ፍየል በምድር ሁሉ ፊት ላይ ወጣ፤ ምድርንም አልነካም፤ ለፍየሉም በዐይኖቹ መካከል አንድ ታላቅ ቀንድ ነበረው።