ዐይኖችንም አቅንቼ አየሁ፤ እነሆም አንድ የበግ አውራ መጥቶ በኡባል አጠገብ ቆመ፤ ሁለት ቀንዶች ነበሩት፤ ቀንዶቹም ረዣዥሞች ነበሩ፤ አንዱ ቀንዱ ግን ከሌላው ቀንዱ ይበልጥ ነበር፤ ረዥሙም ቀንዱ በስተኋላ የበቀለ ነበር።