በራስዋም ላይ ስለ ነበሩ ስለ ዐሥር ቀንዶች፥ በኋላም ስለ ወጣው፥ በፊቱም ስለ ወደቁ ሦስቱ ቀንዶች፥ ዐይኖችና ትዕቢት የተናገረ አፍ ስለ ነበሩት ራሱም ከሌሎች ስለ በለጠ ስለ ሌላው ቀንድ እውነቱን ለማወቅ ጠየቅሁት።