ዳንኤልንም ያንጊዜ ከአንበሶቹ ጕድጓድ አወጣው። ዳንኤልን ይገድሉት ዘንድ የወደዱ እነዚያንም ሰዎች ይዘው በአንበሶች ጕድጓድ ጣሏቸው፤ አንበሶቹም ወዲያውኑ በፊቱ በሉአቸው። ያንጊዜም ንጉሡ፥ “የሚያድን እርሱ ነውና በሰማይና በምድርም ምልክትንና ድንቅ ሥራን ያደርጋልና፥ ዳንኤልንም ከአንበሶች አፍ አድኖታልና ሁሉም የዳንኤልን አምላክ ያምልኩት” አለ።