እነርሱም ከወጡ በኋላ ንጉሡ ለቤል የሚበላውን አዘጋጀ፤ ዳንኤልም ብላቴናውን አመድ ያመጣ ዘንድ አዘዘው፤ በንጉሡ ፊት ብቻ በቤቱ ሁሉ ነሰነሰው፤ ከወጡም በኋላ ደጃፉን ዘግተው በንጉሡ ማኅተም አተሙት።