በተነሣም ጊዜ መንግሥቱ ትሰበራለች፤ በአራቱም ነፋሳት ትበተናለች፤ ለዘሩ ግን አይከፋፈልም፤ ከእርሱም በኋላ እርሱ እንደ ገዛበት አገዛዝ አይሆንም፤ መንግሥቱ ታልፋለች፤ ከእነዚህም ለሌሎች ትሰጣለች።