እርሱም ራሱ ሰው ሆኖ ወደዚህ ዓለም ይመጣል፤ እኔ ሰው ሆኖ ያየሁት፥ ከአባቱም ወደዚህ ዓለም የሚላከው፥ ሰው ሆኖም ወደዚህ ዓለም የሚመጣው፥ እርሱ አብሯቸው ይታይ ዘንድ፥ ይገለጥላቸውም ዘንድ ዐሥራ ሁለት ሐዋርያትን ለእርሱ ይመርጣል፤ ወደ ደብረ ዘይትም ይሄዳል፤ የተራበችንም ነፍስ ሁሉ ያጠግባል።”