ሕዝቡም እንዲህ ሰምተው ወደ እርሱ ሮጡ፤ ኤርምያስንም ወድቆ እንደ ሞተም ሆኖ አገኙትና አለቀሱ፤ ልብሶቻቸውንም ቀደዱ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ፤ መራራ ልቅሶንም አለቀሱ።